Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dmh

Department of Behavioral Health
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

የዲሲ የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት

የተልዕኮ መግለጫ፦

የስነ ባህሪ ጤና መምሪያ (DBH) ተልዕኮ የአእምሮ ጤና ችግር ላለባቸው እና/ወይም በአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነት ምክንያት የሚከሰት የጤና መዛባት ለተከሰተባቸው ህጻናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች አስቸኳይ የስነ አእምሮ ህክምና እርዳታና ማህበረብን መሰረት ያደረገ የተመላላሽ ታካሚዎች ህክምናና ተገልጋዮችን ታሳቢ ያደረጉ፣ ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉና ባህልን ግምት ውስጥ ያስገቡ ተኝተው ለሚታከሙ ሰዎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን እንዲሁም ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት ነዋሪዎችን አጠቃላይ ደህንነት የሚሰጡ ድጋፎችን የሚያጠቃልሉ የመከላከል፣ ፈጣን ምላሽ የመስጠትና የህክምና አገልግሎቶችን መስጠት ነው።

አገልግሎቶች፦

የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት (DBH) ህዝባዊ የስነ ባህሪ ጤና ስርዓት አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ህክምናና አጠቃላይ የአእምሮ ጤና እንዲሁም የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነት የጤና መዛባት አገልግሎቶችንና ድጋፎችን ይሰጣል። የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት (DBH) ከዚህ በተጨማሪም በወንጀል ፍትህ ስርዓት በኩል የተላኩ ግለሰቦችን የጤና ሁኔታ ይመረምራል እንዲሁም ማህበረሰብን መሰረት ባደረጉ ተቋማት ኔትወርክና በልዩ መንግስታዊ አገልግሎት አቅራቢዎች በኩል ለመጡ አዋቂዎች፣ ህጻናትና ወጣቶች እና ለቤተሰቦቻቸው አገልግሎት ይሰጣል።

የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን ማህበረሰብን መሰረት ካደረጉ አገልግሎት አቅራቢዎች በቀጥታ ማግኘት ይቻላል ወይም በ 24/7 አክሰስ ኸልፕ ላይን በ 1(888)7 ወይም 1-888-793-4357 በኩል ማግኘት ይቻላል። በአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚነት ምክንያት ለተከሰተ የጤና መዛባት አገልግሎቶች በስልክ ቁጥር (202) 727-8857 ወደ የምርመራና ሪፈራል ማእከል ይደውሉ። በዚያኑ ቀን የሚሰጥ አስቸኳይ የጤና እርዳታንም ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

የአዋቂዎች አገልግሎቶች

የስነ ባህሪ ጤና አገልግሎቶችንና ድጋፎችን ማግኘት የሚፈልጉ አዋቂዎች ባጠቃላይ ዲስትሪክቱ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ ማህበረሰብን መሰረት ካደረጉ አገልግሎት አቅራቢ የግል ድርጅቶች መካከል የፈለጉትን መምረጥ ይችላሉ። የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት (DBH) እርዳታ በሚሰጡ ተንቀሳቃሽ ቡድኖችና ወደ የማህበረሰብ አገልግሎት አቅራቢዎች በሚሄዱ የቤት አልባዎች እርዳታ አቅራቢ ቡድኖች አማካኝነት ለ24/7 የሚሰራ የአስቸኳይ ስነ አእምሮአዊ ጤና አገልግሎት ተቋምን ያስተዳድራል። የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት (DBH) ከዚህ በተጨማሪ የቅድስት ኤልሳቤጥ ሆስፒታል የዲስትሪክት የውስጥ ታካሚዎች የስነ አእምሮ ጤና አገልግሎት ክፍልን ያስተዳድራል። (LINK)

የህጻናት፣ ወጣቶችና የቤተሰብ አገልግሎቶች

 

የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት (DBH) በቤት፣ በትምህርት ቤትና በማህበረሰቡ ውስጥ ልዩነት መፍጠር እንደሚችሉ የተረጋገጠላቸው በህጻናት እድገት ማእከላት ውስጥ የሚሰጡ የፈጣን ምላሽና የቅድመ መከላከል ስራዎችን፣ በህዝባዊና መንግስታዊ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሰጡ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን፣ የአስቸኳይ እርዳታ ቡድኖችንና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል።  (LINK)

ተጠቃሚዎችና ቤተሰቦች

ማገገምን መሰረት ያደረገው የእርዳታና የራስ ተነሳሽነት ሞዴል ተገልጋዮች ወይም ደንበኞች ከችግራቸው እንዲላቀቁ በሚደረገው ጥረትና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የስነ ባህሪ ጤና አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ መሳተፍና ጥረቱን መምራት እንዳለባቸው የጸና እምነት አለው። የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት (DBH) የአቻ ላቻ የምክክር አገልግሎትን፣ የጤናማ/ከችግር ነጻ የሆነ አኗኗር፣ የችግር አፈታት እቅድና የቤተሰባዊ ድጋፍ ተነሻሽነት እቅዶችን ያዘጋጃል። (LINK)

የትርጉም አገልግሎቶች፦

የመስማት ችግር ካለብዎት ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎ ውስን ከሆነ ወይም ምንም የማይችሉ ከሆኑ ከክፍያ ነጻ ወደሆነው የእርዳታ መጠየቂያ ስልክ ቁጥር 1(888)7 ወይም ወደ ስልክ ቁጥር 1-888-793-4357 ደውለው ጥያቄዎን ያቅርቡ። የመስማት ችግር ላለባቸው ሰዎች ከዚህ በተጨማሪ በቲቲዋይ ስልክ ቁጥር (202) 673-7500 መጠቀም ይችላሉ። ወደ መስሪያ ቤታችን ስልክ ሲደውሉ ወይም ሲመጡ የስታፍ አባላችን እገዛ ከሚያደርግልዎ አስተርጓሚ ጋር እንዳገናኘዎት ያረጋግጡ።

የመገናኛ መረጃዎች፦

ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ከፈለጉ እባክዎ ከክፍያ ነጻ ወደሆነው የእርዳታ መጠየቂያ ስልክ ቁጥር 1(888)7 ወይም በስልክ ቁጥር 1-888-793-4357 ይደውሉ፣ የሚከተለውን ድረ-ገጽ www.dbh.dc.gov ይጎብኙ ወይም በሚከተለው የመልእክት አድራሻ ለዲሲ የስነ ባህሪ ጤና ዲፓርትመንት ደብዳቤ በመጻፍ ጥያቄዎን ያቅርቡ፦ (DC Department of Behavioral Health, 64 New York Avenue, NE, 3rd Floor, Washington, DC  20002)